የመጋቢት 06 ቀን 2011 ዓ.ም የቃል አቀባይ ጽ/ቤት - ሳምንታዊ መግለጫ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የቃል አቀባይ ጽ/ቤት - ሳምንታዊ መግለጫ
በመግለጫው የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች

 1. መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ላይ የደረሰውን የመከስከስ አደጋ የተያያዙ ጉዳዮች
 2. የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት
 3. 6ኛው የኢትዮ-ቱኒዚያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ
 4. የዜጎች ዲፕሎማሲ-በውጭ አገራት በችግር ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ
 5. የኢትዮ-ፈረንሳይ የቢዝነስ ፎረም

1ኛ. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ኢቲ 302 አደጋ ጋር በተያያዘ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ

 • ክስተቱ ከኢትዮጵያውያን አልፎ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ያሳዘነና ልብ የነካ ነው።

 • በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አደጋው በተከሰተበት እለት ኮሚቴ አዋቅሮ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሆን መረጃ የመስጠት ሚናውን ተወጥቷል፤አሁንም በእኛ በኩል ያሉ መረጃዎችን እየሰጠን ነው (ዋናውና ቴክኒካል የሆነው መረጃ በአየር መንገድ በኩል ነው የሚሰጠው)።
        
 • ሰኞ መጋቢት 2 ደግሞ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በጉዳዩ ዙሪያ ከአየር መንገድ ጋር በመሆን ማብራሪያ ሰጥተናል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ

 • በደረሰው አደጋ ከ50 በላይ የአገራት መሪዎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለኢትዮጵያ መንግስት የአጋርነትና የመጽናኛ መልዕክት ልከዋል።
        
 • ከእነዚህ ውስጥም የጎረቤት አገራት መሪዎች ሁሉም፣ የካናዳ፣ የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ፣ የናይጀሪያ፣ የጀርመን፣ የእስራኤል፣ የኳታር፣ የግሪክ፣ የጣልያን ለአብነት ይጠቀሳሉ።

 • በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የአለም ምግብ ድርጅት፣ የአለም የፍልሰተኞች ተቋም፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት፣ የአለም የህጻናት መርጃ ድርጅትና ሌሎች አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ተቋማትም በደረሰው አደጋ ሀዘናቸውን ገልጸው ለተጎጅ ቤተሰቦችና አገራት መጽናናትን ተመኝተዋል።
        
 • አገራት በሚገኙ 60 የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች፣ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ ቤቶችና 14 ቆንስላ ጽ/ቤቶች የሃዘን መግለጫ መዝገብ ለሁለት ቀናት ከፍተው የበርካታ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ሃዘናቸውንና ለኢትዮጵያ ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
       
 • ይህን ተከትሎም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ አስከፊ ወቅት ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን በመቆም ላሳየው አጋርነት መስጋና አስተላልፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ምስጋና ያቀርባል።
2ኛ የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጉብኝት

 • የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። 
 • ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል።
 • ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ የተናጠል ውይይት አድርገዋል።
 • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንና ፕሬዝዳንት ማክሮን በተገኙበት በሁለቱ አገሮች መካካል የመከላከያ ትብብር ስምምነት እና የኢንቨስትመንት ማስፋፋያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
 • በተጨማሪም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን የሚያግዝ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲሁም የቅርስ ጥበቃ ትብብር ስምምነት በሁለቱ መሪዎች ይፋ ተደርጓል።
 • በዚህም በ100 ሚሊዮን ዩሮ የሚያወጣ ብድርና እርዳታ ትብብር ስምምነት ተደርጓል።
 • ፕሬዝዳንት ማክሮን በጉብኝታቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ጋር ተወያይተዋል።
 • ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ኬንያ ናይሮቢ ተጉዘዋል። በኬንያም “የአንድ ፕላኔት ጉባኤ” (One Planet Summit) የሚል መጠሪያ በተሰጠው የአየር ንብረት ጉባኤ ተሳትፈዋል።

3ኛ- 6ኛው የኢትዮ-ቱኒዚያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ

 • 6ኛው የኢትዮ-ቱኒዚያ የሚኒስትቶች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓም በቱኒዚያ ቱኒዝ ተካሂዷል።
 • የኢትዮጵያን ልዑክ የመሩት የኢፌደሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እንዳሉት ኢትዮጵያና ቱኒዚያ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያለቸውና በተለይ አፄ ኃይለስላሴና ፕሬዝዳንት ሀቢብ ቡርጊባ ለአፍሪካ አንድነት መመስረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
 • ሁለቱ አገሮች በቱሪዝም፣ በባህል ፕሮጋራም፣ በኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ፣ በሴቶችና ቤተሰብ እንዲሁም በሙያ ስልጠናና ሥራ መስክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡
 • እነዚህና ካሁን በፊት የተፈረሙት ስምምነቶችም ገቢራዊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው መክረዋል።
 • ኢትዮጵያና ቱኒዚያ የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን የጀመሩት በ1966 ዓ.ም ሲሆን በበርካታ ጉዳዮች በትብብር በመስራት ላይ ይገኛሉ።

4ኛ- የዜጎች ዲፕሎማሲ

 • ኢትዮጵያ ዜጎች በአገራቸው ሰርተው እንዲያተርፉ ትፈልጋለች፤ በውጭ አገራት በተለይ በአረብ አገራት ሄደው እራሳቸውን ለመለውጥ የሚሄዱ ዜጎች ደግሞ ህገ ወጡን መንገድ ትተው በህጋዊ መንገድ እንዲሄዱ ሰፊ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው። (ከኳታርና ሳኡዲ አረቢያ ጋር የተፈረሙት ስምምነቶች ለአብነት ይጠቀሳሉ)
 • ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ሄደው ያለመኖሪያ ፈቃድ በተለያዩ አረብ አገራት ይኖሩ የነበሩ ዜጎቻችን በየአገራቱ ከሚገኙት ቆንስላ ጽ/ቤቶችና ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው እንዲመጡ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
 • ለአብነትም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጅዳ በሚገኘው ቆንስላ ጽ/ቤት በኩል ከሳኡዲ አረቢያ መንግስትና ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመረተባበር ለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 447 ኢትዮጵያዊያንን መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በራሳቸው ፈቃድ ከሳኡዲ አረቢያ እንዲመለሱ አድርጓል።
 • በቀይ ባህር አድርገው በህገ ወጥ መንገድ በሳኡዲ አረቢያ የነበሩ 1800 ኢትዮጵያውያን ከመጋቢት 4-8 ቀን 2011 ዓ.ም ባሉ ቀናት በአራት ዙር ወደ አገራቸው እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ትናንት የገቡትም የዚሁ አካል ናቸው።
 • የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሄራዊ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከታንዛንያ መንግስት ጋር በመተባበር 50 ኢትዮጵያዊያን ታንጋ ከሚባል የታንዛንያ እስር ቤት በትናንትናው ዕለት እለት መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲለቀቁ አድርጓል።
 • ከ450 በላይ በተለያዩ የታንዛንያ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለማስለቀቅ ከታንዛንያ መንግስት ጋር የተጀመረው ድርድር ተጠናከሮ ቀጥሏል።
 • የኢ.ፌ.ደ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ከባለፈው አንድ ዓመት ወዲህ መንግስት ለዜጎች ዲፕሎማሲ በሰጠው ልዩ ትኩረት መሰረት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከተለያዩ አገሮች እስር ቤት እየተለቀቁ ወደአገራቸው እየተመለሱ መሆኑ ይታወቃል።
5ኛ- የኢትዮ-ፈረንሳይ የቢዝነስ ፎረም

 • የኢትዮ-ፈረንሳይ የቢዝነስ ፎረም ዛሬ ከሰዓት ከ9 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ይካሄዳል።
 • ከ26 በላይ አባላት ያለው ታዋቂ የፈረንሳይ የንግድ ልዑክ በአገሪቱ የምስራቅ አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሊቀ መንበር Moman ይመራል፤ በአገራችንም ጉብኝት እያደረገ ነው።
 • በቆይታውም ከኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብና ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ይወያያል።
 • በቢዝነስ ፎረሙ የግልና የመንግስት አጋርነት (Public Private Partnership) ዙሪያ በኢትዮጵያ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች በተለይም በሃይል ማመንጫ፣ በመሰረተ ልማት ዘርፎች ገለጻ ይደረግላቸዋል።
Back to Home

More Trade Events ..

የመጋቢት 06 ቀን 2011 ዓ.ም የቃል አቀባይ ጽ/ቤት - ሳምንታዊ መግለጫ Read More


Read More

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   27
THIS WEEK:   282
THIS MONTH:   65
THIS YEAR:   12351
TOTAL:    34825
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts